ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሞዴልነት ሲገነቡ የቆዩ 105 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እያስመረቁ ነው

96

ነሐሴ 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከ845 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 105 ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን እያስመረቁ ይገኛሉ።

የ60 ቀናት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶቹ ከንቲባዋ በልዩ ሁኔታ ድጋፍ ሲያደርጉበት የቆዩና የመንግስትና የግል በጎአድራጊ ባለሃብቶችን በማስተባበርና በማቀናጀት የተገነቡ ናቸው።

ከፕሮጀክቶቹ መካከልም 244 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የዘመናዊ ቤት ልማት ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባን የቤት ችግር ለመፍታት ትልቅ ተስፋ የተጣለባቸው መሆኑ ተመልክቷል።

May be an image of 1 person

በ69 ቀን ተገንብቶ የተጠናቀቀው እና ለ50 አባወራዎች የቤት ችግርን የሚያቃልለው ባለ 11 ወለል ዘመናዊ ተገጣጣሚ ህንፃ በግንባታ ዘርፉ አዲስ ምእራፍ የከፈተ መሆኑም ተጠቅሷል።

የመኖርያ ቤት ችግርን የሚያቃልሉ 5 ዘመናዊ ህንፃዎች፣ 931 ያረጁና የተጎሳቆሉ ቤቶችን የማደስና የጥገና ስራ ፣ በቀን 2000 ዜጎችን የሚመግቡ 3 ምገባ ማእከላትና 7 የዳቦ ማምረቻና ማከፋፈያ ቦታዎች በዛሬው እለት ለምረቃ ከበቁት ፕሮጀክቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

የትምህርት ቤት ማስፋፍያ ግንባታዎች፣ የፖሊስ ጣቢያ እድሳትና ማስፋፍያ ፣ የመስርያ ሼዶችን እድሳትና የጤና ጣቢያ ማስፋፍያ ግንባታ ፕሮጀክቶችም ይመረቃሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም