የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለጋምቤላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ አደረገ

92

ነሐሴ 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለጋምቤላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣና ለኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስራዎች የሚውል ቁሳቁስና የግብአት ድጋፍ አደረገ።

ሚኒስቴሩ ድጋፉን ያደረገው በእሽ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና የዘላቂ ልማት ፕሮግራም አማካኝነት መሆኑን ገልጿል።

May be an image of 5 people, people standing, indoor and text that says "WING HIWING H"

80 ኮምፒተሮች፣ አራት ሰርቨሮች፣ 20 የውጪ ራውተሮች እና አንድ ዘመናዊ ጀኔሬተር ከተደረጉት ድጋፎች መካከል ይገኙበታል።

የጋምቤላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኒክና የሙያ ስልጠናውን ለማጠናከር በኢትዮጵያ እንዲደገፉ ከተመረጡት 20 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች መካከል አንዱ መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም