በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ለማጠናከር እንደሚሰራ ምክር ቤቱ ገለጸ

163

ነሐሴ 12 ቀን 2014(ኢዜአ) የኢትዮ-አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማሳደግ እንደሚሰራ አስታወቀ።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከምክር ቤቱ የቦርድ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

አምባሳደር ስለሺ ለአባላቱ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰዳቸው ስለሚገኙ የማሻሻያ እርምጃዎች እና ወደ አፍሪካ የእድገትና ዕድል ድንጋጌ (አጎዋ) ተጠቃሚነት በድጋሚ ለመመለስ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በውይይቱ ወቅት የኢትዮ-አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት ያለውን የትስስር አድማስ በመጠቀም የኢትዮጵያን ቢዝነሶች ከአሜሪካ አቻዎቻቸው ጋር በማስተሳሰር ለመስራት ከስምምነት መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተጨማሪም ከኤምባሲው ጋር በቅርበት በመስራት የኢትዮጵያና አሜሪካን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ማሳደግ ላይ እንዲሰራ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም