በሀረሪ ክልል የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለ3 ወራት ተራዘመ

144

ነሃሴ 10/2014/ኢዜአ/ በሀረሪ ክልል የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪንና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተራዝሟል፡፡

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖሪያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

አሁንም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት እንዲራዘም መስተዳድር ምክር ቤቱ ወስኗል።

ስለሆነም በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን የክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት ማሳሰቡን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ አመልክቷል፡፡