በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን እየለማ ካለሁ የኩታ ገጠም እርሻ ከ8 ሚሊየን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ይጠበቃል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

252

ነሐሴ 8 ቀን 2014 (ኢዜአ)በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን እየለማ ካለሁ የኩታ ገጠም እርሻ ከ8 ሚልየን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ በሶማሌ ክልል በፋፈን ዞን ከ127ሺህ ሄክታር የሚበልጥ ኩታ ገጠም እርሻን የጎበኙ ሲሆን ከዚህም ከ8 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል ብለዋል።
ይህ ቀደም ሲል ተዘንግተው የቆዩ ስፍራዎች ወደ ምርታማነት የመለወጣቸው ማሳያ ነው ያሉ ሲሆን እነዚህ ጥረቶች ሊጠናከሩና ሊስፋፉ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም አስተሳሰባችን እና ተግባሮቻችን ሙሉ በሙሉ በምርታማነት እና ልማት ላይ ማተኮር አለባቸው ማለታቸውን ከማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።