በጥቂት ሚሊየኖች ችግኝ መትከልን እንደ ድል በምትቆጥር ዓለም ላይ በአራት ክረምት 25 ቢሊየኖች ማሳካት እንደሚቻል አሳይተንበታል--ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

112

ነሐሴ 8 ቀን 2014 (ኢዜአ) በጥቂት ሚሊየኖች ችግኝ መትከልን እንደ ድል በምትቆጥር ዓለም ላይ በአራት ክረምት 25 ቢሊየኖች ማሳካት እንደሚቻል አሳይተንበታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በድሬደዋ ከተማ በመገኘት አራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በስኬት መከናወኑን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም ወቅት በሀገራችን አረንጓዴ ዐሻራ መጀመሩ ለኢትዮጵያ ሁለት ወሳኝ እድሎችን ፈጥሯል ነው ያሉት።

ይህም አንደኛ በትልቁ አስበን ከተባበርን በትልቁ ማሳካት እንደምንችል ምስክር ሆኖናል ፤ሁለተኛው ለብልጽግና መሠረት የሚሆን ባህል መፍጠሩ ነው ብለዋል፡፡

ችግኝ የመትከል ባህል ሲውል ሲያድር በምግብ ራሳችንን እንድንችል፣ ግድቦቻች ዘላቂ ዝናብ እንዲያገኙ፣ለም አፈራችን እንዳይሸረሸር በማድረግ በድርቅና በርሃብ የጠለሸ የሀገራችን ስም እንዲታደስ በር ይከፍታል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም