አራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ማጠቃለያ መርሃ ግብር በድሬደዋ ከተማ ተከናወነ

210

ነሐሴ 08/2014 /ኢዜአ / አራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ማጠቃለያ መርሃ ግብር በድሬደዋ ከተማ ተከናወነ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፤ በድሬደዋ ከተማ በመገኘት አራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በስኬት መከናወኑን ይፋ አድርገዋል።

በአረንጓዴ አሻራ የተከናወነው የላቀ ስኬትም ኢትዮጵያ የጀመረችውን ማሳካት እንደምትችል ጥሩ ማሳያ ነው ብለዋል።

በአራት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ በተያዘው አቅድ ከ20 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ይህም በሁሉም መስኩ ያቀድናቸውን በመሳካት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ የሚያስችለን ትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆናችንን የሚያመላክት ነው ብለዋል።