የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም መድረክ እየተካሄድ ነው

349

አዳማ ነሐሴ 08/2014 /ኢዜአ / የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም መድረክ በአዳማ በመካሄድ ላይ ነው ።

በመድረኩ የሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ዘሃራ ዑሞዶና ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንድሁም በየደረጃው የሚገኙ የሴቶች ሊግ አመራሮች ተሳታፊ ናቸው ።

የሴቶች ሊግ ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ የሊጉ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ በጥልቀት ይመክራል ተብሏል ።

በተለይ በፓርቲው የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈፃፀምና የተገኙ ውጤቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎትና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑንም ተገልጿል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም