በአፋር ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ከነተጠርጣሪው መያዙን ፖሊስ ገለጸ

147

ነሐሴ 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአፋር ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ከነተጠርጣሪው መያዙን የሰመራ ሎጊያ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያዉ ዋና አዛዥ ኮማንደር ቢልኢ አህመድ እንደገለጹት፤ ገንዘቡ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ነሃሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት ተኩል በከተማዉ ልዩ ስሙ ደረቅ ወደብ በሚባል ቦታ ሊያዝ ችሏል።

May be an image of 1 person and military uniform

ከህብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ መሠረት በተደረገ ክትትል የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2-B34960 አ/አ በሆነ ተሽከርካሪ ተደብቆ 6 ሚሊዮን 738 ሺህ ብር በላይ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ መያዙን ተናግረዋል።

ይህንን ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረው አሽከርካሪ ከነ መኪናው በቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም