አቡበከር ናስር በደቡብ አፍሪካ ሊግ የመጀመሪያውን ግብ አስቆጠረ

1120

ነሐሴ 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) አቡበከር ናስር በዲኤስቲቪ ፕሪሚየርሺፕ የደቡብ አፍሪካ ሊግ የመጀመሪያ ጎሉን አስቆጥሯል።

ዛሬ በሊጉ በተደረገ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታ ማሜሎዲ ሳንዳውንስ ተቀናቃኙን ካይዘር ቺፍስን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ረትቷል።

በቅርቡ ከኢትዮያ ቡና ወደ ማሜሊዲ ሳንዳውንስ የተዘዋወረው አቡበከር ናስር ተቀይሮ በመግባት በጨዋታው አራተኛውና ለራሱ የመጀመሪያውን ግብ በግሩም ሁኔታ አስቆጥሯል።

ፒተር ሻሉሊሌ በጨዋታና ፍጹም ቅጣት ምት እንዲሁም ጋስቶን ሲሪኖ ቀሪዎችን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

አቡበከር ናስር ከቀናት በፊት ማሜሎዲ ሳንዳውንስ ከቲኤስ ጋላክሲ ጋር ባደረገው ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ መሰለፉ የሚታወስ ነው።