የወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

1009

ሆሳዕና፤ ነሐሴ 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) የወራቤ ዩንቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን ከ500 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።

ዛሬ ዩኒቨርሲቲው ያስመረቀው በማህበራዊ፣ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ የትምህርት ክፍሎች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 537 ምሩቃንን ነው።

May be an image of 2 people

ከተመራቂዎች መካከል 21ዱ ምሩቃን በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር ዴኤታና የዩኒቨርስቲዉ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አህመዲን መሀመድን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶች፣ የተመራቂ ተማሪዎች ወላጆችና የአካባቢው ማህበረሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን የኢዜአ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘግቧል።