በክልሉ በ2015 በጀት ዓመት 2ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሠብሰብ ታቅዷል

68

አሶሳ ነሐሴ 06 / 2014 ዓ.ም /ኢዜአ / በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2015 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ አስታወቁ::

የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ለግብር ከፋዮች እና ባለድርሻ አካላት ያዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር ዛሬ በአሶሳ እየተካሄደ ይገኛል::

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ በበጀት ዓመቱ ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል::

በክልሉ በ2015 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል ብለዋል::

በየደረጃው የሚገኙ መንግስታዊ ተቋማት ከሚያደርጉት ጥረት በተጨማሪ በተለይ የንግዱ ማህበረሰብ ግብር የመክፈል ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል::

"ግብር እከፍላለሁ አስከፍላለሁ ህልውናዬን አረጋግጣለሁ" የመርሃ ግብሩ መሪቃል ነው::

መርሃ ግብሩ እስከ ነሐሴ 07 / 2014 ዓ.ም. ይቀጥላል::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም