የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአንድነት ፅናት ምልክት ነው- አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ

151

ጅግጂጋ ፤ ነሐሴ 5/2014(ኢዜአ) ታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአንድነት የፅናት ምልክት ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር : አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ዑመር ገለጹ።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን አስመልክቶ ርዕሰ መስተደድሩ የእንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላልፈዋል።

ባስተላለፉት መልዕክትም ፤  የግድቡ ሁለተኛው ተርባይን  ኃይል ማመንጨት መጀመሩ መላው የሀገራችን ህዝቦች እዚህ ደረጃ እንዲደርስ በፅናትና በትጋት አሻራቸውን አሳርፈዋል ሲሉ አውስተዋል።

ሀገራችን ለዘመናት በደጃፏ ሲፈስ የነበር ወንዛችን ዛሬ ላይ እነሆ ፍሬ አፍርቶ ጨለማ ገፎ ብርሃን ስላሳየን ደስታችን ወደር የለውም ብለዋል ርዕስ መስተዳድሩ።

በአሁኑ ወቅት ምንም እንኳን በጫና ውስጥ ብንሆንም የጀመርነውን ግድባችንን በፅናትና በትጋት አጠናቀን ከሀገራችን አልፈን ሌላውም የአፍሪካ ሀገራት  የብርሃን ምንጭ እንዲሆን የበለጠ መነሳሳት ይኖርብናል ሲሉም ገልጸዋል።