የዱግዳና ቦራ ወረዳ ክላስተር የስንዴ ልማት በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት እየተጎበኘ ነው

133

ዱግዳ ነሀሴ 01/2014 /ኢዜአ /የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳና ቦራ ወረዳ በክላስተር እየለማ ያለውን የስንዴ ማሳ እየጎበኙ ነው።

ፕሬዚዳንቱ የስንዴ ክላስተር ጉብኝታቸውን ቦራ ወረዳ ባርታ ሳሚ ቀበሌ ጀምረዋል ።

በዞኑ ከ280 ሺህ ሄክታር በላይ በተለያዩ ሰብሎች በኩታ ገጠም እየለማ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 188 ሺህ ሄክታሩ በስንዴ ክላስተር መልማቱ ተገልጿል ።

በኦሮሚያ ክልል በእስከ አሁኑ ሂደት ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም በስንዴ ዘር ተሸፍኗል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም