በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የውጭ ሀገር ገንዘብ ተያዘ

215

ሐምሌ 29 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሕብረተሰቡና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረውን የውጭ ሀገር ገንዘብ በዛሬው እለት መያዙን ገለፀ፡፡

በተካሄደው ኦፕሬሽን 27 ሺህ 491 የአሜሪካን ዶላር፣ 15 ሺህ 325 ዩሮ፣ 680 ፓውንድ፣ 6 ሺህ 689 የኤርትራ ናቅፋ፣ 5 ሺህ 200 የሲውዝ ፍራንክ፣ 500 የአንጎላ ክዋንዛ፣ 1 ሺህ 680 የኳታር ሪያል፣1 ሺህ የኖርዌይ ክሮን እና 49 ሺህ 735 የኢትዮጵያ ብር እንዲሁም በርካታ የባንክ ደብተሮች ከ71 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የኢትየጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያመጣው አደጋ ከባድ መሆኑን ተገንዝቡ ሕብረተሰቡ የሚያጠራጥሩ ነገሮችን ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኝ የፀጥታ አካላት በማሳወቅ የተለመደ ቀና ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰቡብ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡