የዩክሬንን እህል የጫነችው መርከብ ቱርክ ወደብ ደረሰች

848

ሐምሌ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ)በግጭቱ ምክንያት ተቋርጦ ከሰሞኑ ግን በሩሲያ እና ዩክሬን ባለስልጣናት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት የዩክሬንን እህል ለተለያዩ ሃገራት ለማድረስ የተንቀሳቀሰችው መርከብ በቦስፎረስ ባህር ወሽመጥ በኩል ቱርክ ግዛት መድረሷን የቱርክ ብሔራዊ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ የሩሲያ እና የዩክሬን ባለስልጣናትን ያካተተ ቡድን መርከቧ ላይ በቱርክ ሜትሮፖሊስ የተደረገውን ፍተሻ ተከትሎ ጉዞው እንደሚቀጥል ገልጿል።
ራዞኒ የተሰኘችው መርከብ ከ26 ሺህ ቶን በላይ በቆሎ ወደ ሊባኖስ እና ትሪፖሊ ታደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።

ጭነቱ የተጫነው በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የእህል እና የማዳበሪያ የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ከስምምነት ከተደረሰ በኋላ መሆኑን የአናዶሉ ኤጀንሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡