ፌዴሬሽኑ በአለም ሻምፒዮናው አመርቂ ውጤት ላስመዘገበው የአትሌቲክስ ቡድን የማበረታቻ ሽልማት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል

320

ሐምሌ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኦሬጎን በተካሄደው 18ኛው አለም ሻምፒዮና ሁለተኛ በመውጣት አመርቂ ውጤት ላስመዘገበው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን በነገው እለት የማበረታቻ ሽልማት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ 4 የወርቅ፤4 የብር እና 2 የነሃስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን መሰብሰቧ ይታወሳል።