ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የቻይና የመከላከያ ሰራዊት ለአለማችን ሰላምና መረጋጋት እያደረገ ላለው በጎ ሚና ያላቸውን አድናቆት ገለጹ

392

ሐምሌ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ሉአላዊነት፣ ፀጥታና ጥቅም ከማስከበር አልፎ ለአለማችን ሰላምና መረጋጋት እያደረገ ላለው በጎ ሚና ያላቸውን አድናቆት ገለጹ።

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የተመሰረተበትን 95ኛ አመት ክብረ በዓል በማስመልከት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ ባስተላለፉት መልዕክት የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ሉአላዊነት፣ ፀጥታና ጥቅም ከማስከበር አልፎ ለአለማችን ሰላምና መረጋጋት እያደረገ ላለው በጎ ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡

ቻይናና ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የዘለቀ ታሪካዊ ወዳጅነት እንዳላቸው አስታውሰው፤ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በመመስረት በሀገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በባህል፣ በትምህርት እና በጤና መስኮች ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡

ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት በወታደራዊ ዲፕሎማሲና ትብብር ላይ ከፍተኛ ዕድገት ላይ እንደደረሱ ገልፀው፤ ሀገራቱ ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝ ማረጋገጣቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም