ከዩክሬን ጥራጥሬ የጫነች መርከብ ወደ ሊባኖስ ታመራለች

630

ሀምሌ 25/2014/ኢዜአ/ ዩክሬን ጥራጥሬ ወደ ውጪ መላክ እንድትችል በቅርቡ በተደረገው ስምምነት መሰረት ኦዴሳ ከተሰኘው ወደቧ ጥራጥሬ የጫነች መርከብ  ወደ ሊባኖስ እንደምታመራ የቱርኪዬ ብሄራዊ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

መርከቧ በፈረንጆች ነሃሴ ሁለት ኢስታንቡል እንደምትደርስ የተነገረ ሲሆን  እስፈላጊው ምርመራ ተደርጎላት ወደ ሊባኖስ የምታመራ ይሆናል ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡

በቆሉ የጫነችውና ከኦዴሳ ወደብ የተነሳችው የሴራሊየን ደረቅ ጭነት አመላላሽ  ራዞኒ የተሰኘችው  መርከብ መዳረሻዋን በሊቢያ ወደብ ሰሜናዊ ሊባኖስ ይሆናል ተብሏል፡፡

ቱርኪዬ፣የተባበሩት መንግስታት ፣ራሺያ እና ዩክሬን  እኤአ ሀምሌ 22/2022 ከሶስት የዩክሬን ወደቦች  ኦዴሳ፣ቼርኖሞርስክ እና የዚኒ ጥራጥሬን ለማመላለስ ክፍት እንዲሆኑ መስማማታቸው ይታወቃል፡፡

ወደቦቹ  ስድስት ወራትን ባስቆጠረው በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት  ዝግ ሆነው መሰንበታቸው ታውቋል፡፡

የዩክሬንን የጥራጥሬ የወጪ ንግድ ለማሳለጥ በኢስታንቡል ማእክል የተቋቋመ ሲሆን የቱርኪዬ፣የተባበሩት መንግስታት ፣የራሺያ እና ዩክሬን  ተወካዮች በተገኙበት ስምምነት ተፈፅሟል፡፡

ስምምነቱ የዩክሬንን ደህንነቱ የተጠበቀ የመርከብ  ትራንስፖርትን ለማሳለጥ ፣የንግድ መርከቦች እና ምግብና ሸቀጦች አንዲሁም ማዳበሪያን ከሶስቱ ወደቦች ለማንቀሳቀስ ያግዛል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ የመርከቧን ከወደብ መነሳት አስመልክተው ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡

የመርከቧ መነሳት የስምምነቱን ውጤታማነት እንደሚያመላክት ታውቋል፡፡

መርከቧ 26ሺህ 527 ቶን በቆሎ የምታጓጉዝ ሲሆን ስምምነቱ ከተፈረመ በኀላ የመጀመሪያ ጉዞ ሲሆን ጭነቱ ወደ አለም አቀፍ ገበያ በመግባት ሰብአዊ ፋይዳው  የጎላ ነው ተብሏል፡፡

በተሰጠው አመራር ቱርክዬን ያመሰገኑት አነቶኒዮ ጉተሬዝ  በስምምነቱ መሰረት ተጨማሪ የንግድ መርከቦች እንደሚጓጓዙ ተስፋቸውን ገልፀው  የሰብአዊ ቀውስን በማስታገስ  የአለምን የምግብ ደህንነት ያረጋጋል  ማለታቸውን አናዶሉ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም