የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ለአፋር ክልል ጦርነት ተጎጂዎች ከአምስት ሚሊየን ብር ደገፈ

119

ሀምሌ 18/ኢዜአ/ የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በአፋር ክልል የጦርነት ተጎጂዎች ከአምስት ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ ።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋናን ጨምሮ የሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሸራተኞች በአፋር ክልል ኢሊ ውሃ ከተማ ላይ ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውንም አስቀምጠዋል።

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እና ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመሆን ነው የተለያዩ ድጋፎችን ያደረጉት።

ከድጋፎቹ መካከልም ለ300 የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የአንድ ዓመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ይገኝበታል።

በተጨማሪም በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የዕለት ደራሽ ምግብ ነክ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል።

የአሸባሪው የሕወሀት ቡድን ከፍተኛ ውድመት ባደረሰባት ካሳጊታ ከተማ በጦርነት የወደሙ 10 ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ስራም ጀምረዋል።

በዚህች ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሕልውና ዘመቻውን መምራታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም