በጉራጌ ዞን ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባው የአገና መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመረቀ

336

ሐምሌ 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) በደቡብ ክልልጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት የተገነባው የአገና መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመረቀ።
ሆስፒታሉ በእዣ ወረዳና አካባቢው ለሚገኙ ከ120 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች አገልግሎት በመስጠት ከጤና ተቋማት ግንባታ ረገድ ለረጅም ጊዜ ሲነሳ የነበረውን የአካባቢውን ማህበረሰብ ጥያቄ ይመልሳል ነው የተባለው።
በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ፤ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማህመድ ጀማል ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፤ ባለሙያዎች፤የአገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም