ሦስት የቻይና ኩባንያዎች በአዲስ አበባ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች እድሳት አስጀመሩ

86

ሐምሌ 16 ቀን 2014(ኢዜአ) በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ሦስት የቻይና ኩባንያዎች በአዲስ አበባ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች እድሳት አስጀመሩ።

ኩባንያዎቹ እድሳቱን ያስጀመሩት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሚገኙ የ12 የአቅመ ደካማ ወገኖችን መኖሪያ ቤቶች ነው።

በማስጀመሪያ መርሐግብሩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የቻይና ኢምባሲ የንግድና ኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ ያንግ ይ ሀንግ፤ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት በማገዝ ቻይና ሁል ጊዜም ከጎኗ መሆኗን ገልጸዋል።

May be an image of 1 person

በኢትዮጵያ በተለያዩ የኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩት ሶስት የቻይና ኩባንያዎች በአዲስ አበባ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች ገንብቶ ለማስረከብ ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የቻይና ኩባንያዎች የስራ እድሎችን ከመፍጠር ባለፈ በማህበራዊ ሃላፊነት በርካታ ተግባራትን እየከወኑ መሆኑንም ጠቅሰው ቻይናና ኢትዮጵያ የረጅም ዓመታት የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ወዳጅ አገሮች እንደመሆናቸው በሁሉም መስክ ትብብራቸው ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

በርካታ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የተለያዩ የልማት ስራዎች በመሳተፍ ለስራ እድል ፈጠራና ለአገሪቱ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ስለመሆናቸውም ጠቅሰዋል።

የቤት እድሳት መርሐግብሩን ያስጀመሩት የቻይና ኩባንያ የስራ ሃላፊዎች ቤቶቹን በፍጥነትና በጥራት ገንብተን ለማስረከብ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ፤ የቻይና ኩባንያዎች ከልማት ስራቸው በተጓዳኝ በማህበራዊ ሃላፊነት በመሳተፋቸው አመስግነዋል።

May be an image of 1 person

የስራ ዕድል መፍጠር፣ የውጭ ገቢን ማሳደግ እና የህብረተሰቡን ህይወት የሚለውጡ ስራዎችን መስራት ኢንቨስተሮች አንደኛው ግዴታ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የቤት እድሳቱ የተጀመረላቸው ነዋሪዎች መደሰታቸውን ገልጸው በዚሁ መልካም ተግባር ላይ ለተሳተፉ ሁሉ አመስግነዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም