ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ አጀንዳዎችን በብሪክስ ማቅረቧን እንደምትቀጥል አስታወቀች

106
መስከረም 5/2010 ደቡብ አፍሪካ እንደበፊቱ ሁሉ የአፍሪካ ጉዳዮችን በብሪክስ አጀንዳዎች እንዲያዙ እንደምትሰራ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ አስታወቁ፡፡ ብሪክስ  በተፋጠነ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚገኙ ብራዚል ፣ ሩሲያ ፣ህንድና ፣ቻይና የመሰረቱት የኢኮኖሚ ትብብር  ሲሆን ከአፍሪካ ደቡብ አፍሪካ አባል ነች፡፡ ራማፎሳ ይህን ያሉት በፕሪቶሪያ የዲፕሎማቲክ አባላትን ባነጋገሩበት ወቅት ሲሆን ደቡብ አፍሪካ አባል በሆነችባቸው ተቋማት ለአፍሪካ አህጉር ቅድሚያ ሰጥታ ትሰራለች ብለዋል፡፡ “ደቡበ አፍሪካ ብሪክስን ከተቀላቀለች ጀምሮ ስትራቴጂ በመቀየስ በብሪክስ አጀንዳዎች አፍሪካ እንድትያዝና የብሪክስ አጋሮች ለአፍሪካ ኢንደስትሪና መሰረተልማት  ድጋፍ እንዲያደርጉ አየሰራን ነው” ብለዋል ራማፎሳ፡፡ ራማፎሳ እንዳሉት የብሪክስ የመጀመሪያዎቹ አስርት ዓመታት ስኬት አዲስ የልማት ባንክ ማቋቋሙና በአፍሪካም ይህን ማእከል መክፈቱ ነው፤ ይህም ለፕሮጀክት ፈንድ የሚያጋጥመውን ችግር አቃሏል፡፡ ደቡብ አፍሪካም የብሪክስን ትብብር ስትቀላቀል ባንኩ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ልማቶች ያለውን ሚና እንዲያስፋፋ ስትንቀሳቀስ ነበር ብለዋል፡፡ ራማፎሳ እንዳሉት ባለፈው ሀምሌ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 10ኛው የብሪክስ ጉባኤ ጥቂት የአፍሪካና ታዳጊ ሃገራት በብሪክስ ፕላስ ፎርማት መሰረት ተሳትፈዋል፤ የታዳጊ ሃገራቱም አጀንዳዎች አለም አቀፍ ቅርፅ እንዲይዙ መስራት ይገባቸዋል ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም