ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የውጭ አገራት ገንዘብና 6 ሺህ 84 ነጥብ 82 ግራም ወርቅ ተያዘ

249

ሐምሌ 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) 24 ሚሊዮን 339 ሺህ 280 ብር ግምት ያለው የውጭ አገራት ገንዘብ እና 6 ሺህ 84 ነጥብ 82 ግራም ወርቅ ተያዘ።

መነሻዉን አዲስ አበባ አድርጎ መድረሻዉን ሐረር ከተማ ለማድረግ አስቦ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2አአ B33202 መኪና ቀረሳ ኬላ ሲደርስ በቀን 13/11/14 ዓ፡ም ከቀኑ 6:00 ሲል ሐረር ከተማ ሲደርስ ከሐረር ከተማ ፖሊስ ጋር በመሆን የአሜሪካና የካናዳ ዶላር፣ የእንግሊዝ ፓውንድ፣ የሳዑዲ ሪያል እና 6 ሺህ 84 ነጥብ 82 ግራም ወርቅ ከነ አዘዋዋሪዎቹ ተይዟል።

የተያዘው የውጭ አገሮች ገንዘብ 182 ሺህ 675 የአሜሪካ ዶላር፣ 5 ሺህ 530 የካናዳ ዶላር፣ 1 ሺህ 800 ፓዉንድ 67 ሺህ 145 የሳኡዲ ሪያል ከ ሁለት አዘዋዋሪዎች ጭምር በቁጥጥር ስር እንዲዉል ተደርጓል፡፡

በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የተያዘው ገንዘብና ወርቅ ወደ ኢትዮጰያ ብር ሲቀየር 24 ሚሊዮን 339 ሺህ 280 ብር እንደሚሆን ምንጮቻችን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም