የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወደ አገሩ ገባ

81
አዲስ አበባ መስከረም 5/2011 በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) አመራር ወደ አገር ገባ፡፡ የአመራር ቡድኑ ከሁለት አስርተ ዓመታት የስደትና የትጥቅ ትግል በኋላ ዛሬ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ካንቲባ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ አባ ገዳዎች፣ እንዲሁም የፓርቲ አመራሮችና ደጋፊዎቹ አቀባበል አድርገውለታል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም