አሸባሪው ህወሃት በአፋር ክልል ጉዳት ላደረሰባቸው ወገኖች ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

165

ሠመራ ፤ ሐምሌ 14/2014 (ኢዜአ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአፋር ክልል ወረራ በፈጸመበት ወቅት ጉዳት ላደረሰባቸው ወገኖች ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ።

በአሜሪካ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን  የተሰበሰበውን ይህንኑ ድጋፍ  የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ለአፋር ክልል  ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አወል አርባ  ዛሬ አስረክበዋል።

በተጨማሪም “በድር ” ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት አመራሮችም በዕለቱ የ1ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ  ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ