ለትምህርት ቤቱ ከ1 ሚለዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ

99

ሆሳዕና፣ ሐምሌ 9/2014 (ኢዜአ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ ለዌራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1 ሚለዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የትምህርት ቁሳቁሶችን በድጋፍ አበረከቱ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበልና የተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች  በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ በመገኘት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር ዛሬ አስጀምረዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት ለትምህርት ቤቱ በድጋፍ ካበረከቷቸው ቁሳቁሶች መካከል ኮምፕዩተሮች፣ ፕርንተሮች፣ ደብተሮችና ሌሎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ይገኙበታል ።

በትምህርት ቤቱ ግንባታቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ የትምህርት ክፍሎችን ለማጠናቀቅ ድጋፍ እንደሚደረግ ተመላክቷል ።

በስነ ስርአቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፣ የተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።

እንዲሁም የደቡብ ክልልና ሀዲያ ዞን የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የአከባቢው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም