ከውጭ የሚገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀጣይ ጉዞ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አንደበት

62
አዲስ አበባ መስከረም 3/2011 ከሰሞኑ የተሰናበትነው የ2010 ዓመት አመሻሽ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ዑደት ለየት ያለ ስፍራ ጥሎ ያለፈ ወቅት ነበር። በሰላማዊም ይሁን ነፍጥ አንግበው በውጭ አገራት ትግል ላይ የቆዩ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰላማዊ ጥሪ አገር ውስጥ ተፎካክረው ለመወዳደር ወደ አገራቸው ገብተዋል፤ በመግባት ላይም ናቸው። በ2011 አዲስ ዓመት ዋዜማ በነበረው የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ ምሽትም በተለያዩ የአስተሳሰብ ጎራዎች የተሰለፉ የፓለቲከ ድርጅት መሪዎች በአንድ መዓድ ተሰልፈው ተስተውለዋል። ኢትዮጵያም እጆቿን ዘርግታ መላውን ልጆቿን ሰብስባ ወደ ተስፋ አቅንታለች። በዕለቱ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በስፍራው ተገኝተው ሁነቱን የታዘቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ከውጭ ወደ አገር ቤት የገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃሳብ ፉክክር ለአገር አንድነት፣ ሰላምና ብልጽግና በጋራ መስራት ቀጣይ የቤት ስራቸው ሊሆን እንደሚገባ ይናገራሉ። በዚህም በሚያራምዱት አገራዊ አስተሳስብ በውይይትና በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ለአገርና ለህዝቦች ሰላምና መረጋጋት ይበልጡኑ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ነው የተናገሩት። የፖለቲካ ፓርቲዎች በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሃሳብን በሃሳብ ማንሸራሸሩን ባህል ይዘው እርስ በራሳቸው ተከባብረው የሚነቋቆሩ መሆን አስፈላጊ አይደለም ያሉት  ዶክተር ሔለን ተስፋዬ  ናት ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ካደረገው ነገር ሁሉ የተሰደዱ የፖለቲከ ድርጅቶችን የአገር ጉዳይ በጋራ ተነጋግረው በጋራ ለመስራት ያደረጉት ጥረት ምስጋና ሊቸረው ይገባል የሚሉት ደግሞ አብዱራህማን ሰዓዶ ናቸው፡፡              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም