ሠላምን በዘላቂነት ለማስፈን የዴሞክራሲ ተቋማት ራሳቸውን በሠው ኃይልና በለውጥ አደረጃጀቶች መገንባት ይጠበቅባቸዋል-አቶ ታገሠ ጫፎ

165

ሐምሌ 4 ቀን 2014(ኢዜአ) ሠላምን በዘላቂነት ለማስፈንና ልማትን ለማረጋገጥ የዴሞክራሲ ተቋማት ራሳቸውን በሠው ኃይልና በተቋም የለውጥ አደረጃጀት በሰፊው መገንባት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ አሳሰቡ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያዘጋጀው የዲሞክራሲ ተቋማት የሆኑት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ የፌደራል ኦዲተርና የመገናኛ ብዙኃን የማሻሻያ የለውጥ ስራዎችን የተመለከተ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በዚህ ወቅት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ የዴሞክራሲ ተቋማት ምክር ቤቱ በሕገ መንግስቱ የተሰጠውን ስልጣን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ክንፎች ናቸው ብለዋል።

May be an image of 8 people, people sitting, people standing and indoor

ተቋማቱ የሰብአዊ መብት መጠበቅን ለማረጋገጥ ፣አስተዳደራዊ በደሎችን ለመቅረፍ፣የሀብት አስተዳደርን በአግባቡ ለመጠቀምና የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለመገንባት እንዲሁም የህዝብ ድምጽን ለማሰማት እነዚህ ተቋማት ወሳኝ ናቸው ነው ያሉት።

ተቋማቱ በሀገሪቱ ለተከናወኑ የለውጥ ስራዎች ከፍተኛ አቅም ሆነዋል ያሉት አፈ ጉባኤው ሠላምን በዘላቂነት ለማስፈንና ልማትን ለማረጋገጥ የዴሞክራሲ ተቋማት ራሳቸውን በሠው ኃይልና በተቋም የለውጥ አደረጃጀት በሰፊው መገንባት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

በጥቂት ጸረ ሰላም ኃይሎች የሚፈጸሙ ችግሮችን በአንድነት በመቆምና ህመሙን በጋራ በማከም መፍትሔ ማምጣት ይጠበቅብናልም ብለዋል።

No photo description available.

በየትኛውም ጊዜ አብሮ መቆም የታሪክ አካላችን ነው ያሉት አፈ-ጉባኤው በአንድነት በመቆም ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፣የፌደራል ኦዲተር፣ የመገናኛ ብዙኃንና የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ተቋማቱም ያከናወኗቸውን የለውጥ ስራዎች በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም