ሩስያ በአርክቲክ ውቅያኖስ አካባቢ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ማግኘቷን አስታወቀች

507

ሐምሌ 03 ቀን 2014(ኢዜአ) የሩስያ ጉዙፉ የሃይል አቅራቢ ሮዝኒፍት በአርክቲክ ውቅያኖስ አካባቢ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት መገኘቱን አስታውቋል።

ሮዝኒፍት እንደገለጸው በአትላንቲክ ውቅያኖስ አካባቢ ፔቾራ በተባለው ባህር 82 ሚሊዮን ቶን የሚገመት የነዳጅ ክምችት ተገኝቷል።

አሁን ተገኘ የተባለው ነዳጅ በቅርብ ጊዜ ከተገኙ የነዳጅ ከምችቶች በእጅጉ ከፍተኛ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በየቀኑ 220 ኪዩቢክ የፍሰት መጠን እንዳለው ተነግሯል።

May be an image of ocean and nature

ነዳጁ በተገኘበት አካባቢ የበለጠ ጥናት በማድረግ አካባቢውን ለማልማትና ተጨማሪ ቦታዎችን ለመዳሰስ በሰፊው እንደሚሰራ አርቲ ዘግቧል።

ሮዝኒፍት በአትላንቲክ በሚገኙ 28 ቦታዎች የነዳጅ ማውጣት ፍቃድ የተሰጠው ሲሆን 8ቱ ፔቾራ በተባለው ባህር አካባቢ የሚካሄዱ መሆናቸው ተመልክቷል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ