ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ 4ተኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልል ደረጃ በኢሉ አባቦር ዞን አስጀመሩ

198

ሰኔ 26 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ 4ተኛውን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በክልል ደረጃ በኢሉ አባቦር ዞን ያዮ ወረዳ አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት በተያዘው አመት በክልሉ እስካሁን 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር የተሰራውን ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል የደን ሽፋንን ለማሳደግ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

አክለውም የያዮ ደን የኦሮሞ ህዝብ የተፈጥሮ ሃብቶችን በተለይም የደን እንክብካቤ ላይ ያለውን ባህል እሴት በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል።

በኢሉባቦር የዞኑን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ ተናግረዋል።

May be an image of 8 people, people standing and grass

በዞኑ ያለውን የያዮ ደን በማልማት ከካርቦን ሽያጭ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት እና የአካባቢውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ አበራ ወርቁ በበኩላቸው ባለፉት ሶስት አመታት በክልሉ 9 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል መቻሉን ገልጸው ከዚህ ውስጥ ከ7 ቢሊዮን በላይ መፅደቁን ገልፀዋል።

አረንጓዴ አሻራ የአርሶ አደሩን ምርት እና ምርታማነት በማሳደግና የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ጎልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።

በዚህ አመትም ከባለፈዉ ውስንነት በመማር 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን የተለያዩ ጥቅም ያላቸው ችግኞችን ለመትከልዝግጅት መደረጉን የኦቢኤን ዘገባ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ