ከ455 ሺህ 400 በላይ መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ መፃህፍት ተሰበሰበ

114

ሰኔ 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የሚያስፈልጉ መጻሕፍትን ለማሰባሰብ በተካሄደው ዘመቻ ከ455 ሺህ 400 በላይ መጻሕፍት ተሰበሰበ።

በመጻሕፍት ማሰባሰብ ዘመቻ የመጀመሪያ ምዕራፍ ህብረተሰቡ፣ የተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የነቃ ተሳትፎ አድርገዋል።

ሚሊዮን መጻሕፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ የመጽሐፍ ማሰባሰብ የመዝጊያ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

በዚሁ ወቅት የተለያዩ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መገናኛ ብዙሃን እና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

May be an image of 3 people and people standing

የመጻሕፍት ማሰባሰቡ ሂደት ወደፊት የሚቀጥል ሲሆን ህብረተሰቡ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

የመጀመሪያ ምዕራፍ መጻሕፍት የማሰባሰብ መርሃ ግብር ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

የመጻሕፍት ማሰባሰብ መርሃ-ግብሩ "ሚሊዮን መጽሐፍት ለሚሊዮን ትውልድ" በሚል የተካሄደ ሲሆን፤ ዛሬ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቋል።

የመርሃ ግብሩ ዓላማ ለቤተ-መጻህፍቱ የሚውሉ መጻሕፍት በዓይነትና በብዛት ማሰባሰብ የነበረ ሲሆን የተለያየ ይዘት ያላቸው መጻሕፍት ሊሰባሰቡ ችለዋል።

May be an image of 10 people

ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ በዘመናዊ መልኩ የተገነባው ቤተ መፃህፍቱ ሶፍት ኮፒን ጨምሮ ከ4 ሚሊዮን በላይ መጽሀፍት የመያዝ አቅም አለው።

ቤተ-መጻሕፍቱን በመጻሕፍት ለመሙላት ለቀጣይ አንድ ወር በሚቆየው መርሃ ግብር ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

የአብርሆት ቤተ መጽሃፍት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ ም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም