የደምብ ማስከበር ባለስልጣን በክረምቱ የአቅመ ደካማና አረጋዊያን ቤቶችን እድሳት ጀመረ

128

ሰኔ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደምብ ማስከበር ባለስልጣን በክረምቱ የአቅመ ደካማና አረጋዊያን ቤቶችን እድሳት ጀመረ።

በሁሉም ክፍለ ከተሞች የ121 ወገኖችን መኖሪያ ቤቶች ለማደስ ያቀደ ሲሆን ስራውን በዛሬው እለት በአቃቂ  ቃሊቲ  ክፍለ ከተማ አስጀምሯል።

የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፤ የደንብ ጥሰትን ከመከላከል ባለፈ በክረምቱ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከባለስልጣኑ  ሰራተኞች  ባለሀብቶችና  ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች በሚሠበሠብ  ገንዘብ በክረምቱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የ121 ችግረኛና አቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት እድሳት ማስጀመሩን ገልጸዋል።

የቤት እድሳት መርሃ ግብሩ በአቃቂ  ቃሊቲ  ክፍለ ከተማ በወረዳ  9 እና 1 በዛሬው እለት በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የከተማ  አስተዳደርሩ የሠላምና ጸጥታ ምክትል ቢሮ  ሃላፊ  ሊዲያ ታደሠ፤  ባለስልጣኑ ከደንብ ማስከበር ስራው ባለፈ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ በመሆኑ አመስግነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደምብ ማስከበር ባለስልጣን ሰራተኞች በትናንትናው እለት በመስቀል አደባባይ የደም ልገሳ ማድርጋቸው ይታወቃል።