የበጎ ፈቃድ እና ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሐረሪ ክልል እየተካሔደ ነው

119

ሰኔ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ)የወጣቶች የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ እና ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሐረሪ ክልል እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዲሁም ከፍተኛ የፌዴራል እና ክልል መንግስት የስራ ሃላፊዎች፣የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ‘’በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ’’ በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሔደ የሚገኘው፡፡