የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው

ሰኔ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን “የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን እየታገልን የዴሞክራሲ ስርዓትን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡

የውይይቱ ዓላማ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ የመጣውን የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል በሚያስችሉ መንገዶች ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቶ መፍትሔ ለማበጀት መሆኑ ተመልክቷል።

ከባለስልጣኑ እንደተገኘው መረጃ መድረኩ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመከላከል ረገድ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንዲሁም ሀገራዊ ንቅናቄ እንዲፈጠር ለማድረግ የታሰበ ነው፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም