የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አንደኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

80

ሀዋሳ፣ ሰኔ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አንደኛ ጉባኤ “የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና ” በሚል መሪ ሀሳብ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሠረት መስቀሌ፣ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ከየክልሉ የመጡ የሊጉ አመራሮች ተገኝተዋል።

እስከ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው የሊጉ ጉባኤ በተለያዩ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል ።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ