እምነት፣ ብሔርና የፖለቲካ አመለካከት አንድ ሆነን ከመኖር እንደማያግዱን የአውራ አምባ ማኅበረሰብ ህያው ምስክር ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

170

ሰኔ 21 ቀን 2014 (ኢዜአ) “እምነት፣ ብሔርና የፖለቲካ አመለካከት አንድ ሆነን ከመኖር እንደማያግዱን የአውራ አምባ ማኅበረሰብ ህያው ምስክር ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመቱን እያከበረ ለሚገኘው የአውራ አምባ ማህበረሰብ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም “የጾታ እኩልነት፣ የሕጻናትና የአካል ጉዳተኞች ማኅበራዊ ፍትሕ በተግባር ተፈትኖ ያየንበት ማኅበረሰብ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ሃምሳ ዓመት በእነዚህ ዕሴቶች ጸንቶ መኖር ድንቅ ብቻ ሳይሆን ተአምርም ነው” ብለዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤