ጆርጅ ዊሃ ላይቤሪያ ከናይጀሪያ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ተሰልፎ በመጫወቱ የበርካቶችን ቀልብ ስቧል

1237

መስከረም 2/2011ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ ላይቤሪያ ከናይጀሪያ ጋር ባደረገችው የእግር ኳስ ጨዋታ ተሰልፎ መጫወቱ የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።

ትናንት ምሽት በሞኖሮቪያ በተደረገው የላይቤሪያና የናይጀሪያ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ በ51 ዓመት እድሜው ለሀገሩ ተሰልፎ ተጫውቷል።

የቀድሞው ዝነኛ የእግር ኳስ ተጫዋችና የአሁኑ የሀገር መሪ ዊሃ ለ79 ደቂቃዎች ተሰልፎ ተጫውቷል።

ዊሃ ተቀይሮ ከሜዳ ሲወጣም  የስታዲየሙ ታዳሚዎች አድናቆታቸውን በደማቅ ጭብጨባ ገልጸውለታል።

በትናንት ጨዋታ ላይቤሪያ በናይጀሪያ 2 ለ 1 ተሸንፋለች።

የቀድሞው የኤሲ ሚላን አጥቂ እና ዝነኛው አፍርካዊ ተጫዋች ዊሃ ባለፈው ዓመት ጥር ወር የላብሪያ ፕሬዚዳንት ሆኖ መመረጡ ይታወሳል።

የመጀመሪያው አፍሪካዊ የፊፋ የዓለም ምርጥ ተጫዋችነት ሽልማትን ያገኘ ዝነኛ የእግር ኳስ ተጫዋች መሆኑ ይታወቃል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ