የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አባላት አረንጓዴ አሻራቸውን እያኖሩ ነው

143

ሀዋሳ ሰኔ 21/2014 (ኢዜአ)የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አንደኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች በሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ የአረንጓዴ አሻራቸውን እያኖሩ ነው ።

አሞራ ገደል ተብሎ በሚጠራው የሀዋሳ ሐይቅ ዳር እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አሻራቸውን እያኖሩ ያሉት የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አባላት ናቸው።

የፓርቲው ሴቶች ሊግ አንደኛ ጉባኤ ለመሳተፍ ሀዋሳ የገቡት አባላት ባካሄዱት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ ተገኝተዋል።

የፓርቲው ሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሠረት መስቀሌ፣ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እንዲሁም ከየክልሉ የተውጣጡ የሊጉ አባላትና ሌሎች እንግዶችም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን እያካሄዱ ነው።

የፖርቲው ሴቶች ሊግ የመጀመሪያ ጉባኤ “የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ በሀዋሳ ከተማ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።