ብሔራዊ የግጭት መከላከልና የሰላም ግንባታ ስትራቴጂ ተዘጋጀ

209

ሰኔ 21 ቀን 2014 (ኢዜአ) ብሔራዊ የግጭት መከላከልና የሰላም ግንባታ ስትራቴጂ መዘጋጀቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ።

በኢትዮጵያ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያግዝ ብሔራዊ  የግጭት መከላከልና የሰላም ግንባታ ስትራቴጂ ተዘጋጅቷል።

በስትራቴጂው ዙሪያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር፤ መልኩን እየቀያየረ የሚከሰተውን ግጭት ቀድሞ ለመከላከል አሰራራ መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ግጭቶችን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ባይቻልም መንስኤዎችን በማጥናትና ቀድሞ በመከላከል ለመፍትሔው መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመሆኑም በዚሁ ዙሪያ የተዘጋጀውን ስትራቴጂ ለማጎልበትና በመከላከል ሂደቱ ላይ ለመምከር የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም