"ስለ ኢትዮጵያ" የፓናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ በአርባምንጭ ከተማ ተጀመረ

95

አርባምንጭ፣ ሰኔ 21 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዘጋጅነት የሚካሄደው ''ስለ ኢትዮጵያ'' የፓናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ በአርባምንጭ ከተማ ተጀመረ፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፕሮፈሰር በየነ ዼጥሮስ ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰን ጨምሮ የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ምሁራን፣ የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሐ ግብሩ ላይ እየተሳተፉ ነው።

በሰላም፣ ዴሞክራሲና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

በ1950ዎችና 60ዎች የነበረውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ለሀገር ሉዓላዊነት የተከፈሉ መስዋዕትነቶችና በፌዴራሊዝም ጉዞ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሀገራዊ ሁነቶችን የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውደርዕይም ለተመልካች ክፍት ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ12 ከተሞች የፓናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ለማካሄድ አቅዶ እየሰራ ሲሆን ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው አምስተኛው መሆኑ ተመላክቷል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም