የአዲስ አበባ 4ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተጀመረ

383

ሰኔ 21 ቀን 2014(ኢዜአ) የአዲስ አበባ 4ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

በስነስርዓቱ ላይ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፤ የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን ፤ የሴቶችና ህፃናት ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ፤የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የከተማዋ ከፍተኛ መንግስት የስራ ሃላፊዎች አርበኞች፣ አርቲስቶችና ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ባለፉት ሶስት አመታት ከ26ሚሊየን በላይ ችግኝ በመትከል ለአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ስኬት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዛሬው እለት 30ሺህ ችግኞች ይተከላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም