ኢትዮጵያ በፖለቲካ አመለካከት መታሰርና መሳደድ አብቅቶ ሁሉም በነጻነት የሚኖርባት አገር ትሆናለች

71
አዲስ አበባ መስከረም 1/2011 ኢትዮጵያ በፖለቲካ አመለካከት መታሰርና መሳደድ አብቅቶ ሁሉም በነጻነት የሚኖርባት አገር እንደምትሆን ከተለያየ አካባቢ የአዲስ አመት ዋዜማን ለማክበር በሚሌኒየም አዳራሽ የተገኙ ታዳሚዎች ገለጹ። "በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ትናንት በተካሄደው የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ መርሃ-ግብር  ፕሮግራም የታደሙ ኢትዮጵያውያን በአገሪቱ የነፈሰው የለውጥ ንፋስ ተስፋ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። በአዲስ አመት ታላቋን ኢትዮጵያ በጋራ ለመገንባት በፍቅር ተደምረው በይቅርታ ለመሻገር መዘጋጀታቸውንም ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የመደመር እሳቤን በተግባር ለመተርጎም ከቂም፣ በቀል እና ጥላቻ ተላቀው ከወዳጅ፣ ዘመዶችና ጎረቤቶች ጋር በመተሳሰብ ለመኖር ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።  የጎንደሩ ወጣት ብርሃኑ ይመር እንደሚለው"በፍቅር ተደምረን በይቅርታ እንሻገር መልዕክቱ ለእኔ በጣም ብዙ ነው። ባለፈው ዓመት ከፍተኛ የሆነ የብሄር፣ ጎሳ፣ የሀይማኖትና እንዲሁም በርካታ ግጭቶች አሳልፈናል።በርካታ ወገኖቻችን በህይወት አተናል ይህን ችግር ቀርፈን በፍቅር የምንደመርበት ግዜ በመምጣቱ በደሰቱን ተናግሯል፡፡  በአዲስ አመት ፍቅርን ለመጀመር ከጎረቤቶቻችን አንስቶ የተኮራረፍን በይቅርታ በአዲስ መንፈስ ተደምረናልየምትለው ደግሞ የአዲስ አበባ  ነዋሪዋ ወይዘሮ ፋናዬ ፈጠነ ናት፡፡  ከደቡብ ክልል ከኮንታ ልዩ ወረዳ የመጣው  አቶ ብርሃኑ ጠላ በበኩሉ "እኔ እንደ አንድ ግለሰብ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ ባለኝ አቅም ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ውጤት ለማምጣት በመደመር በይቅርታ ለመሻገር የሚያስፈልገውን ሁሉ አደርጋለሁ።" ፍቅር መስጠትና ይቅርታ ማድረግ ኢትዮጵያዊ ባህልና ጨዋነት በመሆኑ በአዲሱን ዓመት በፍቅር በመደመርና በይቅርታ በመሻገር ታላቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ገልጸዋል።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም