የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አቴንስ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ቁጥር አሳደገ

122

ሰኔ 18 ቀን 2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ግሪክ አቴንስ የሚያደርገውን በረራ በመጨመር በሳምንት ሶስት ጊዜ መብረር መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ብሩ አረጋግጠዋል።

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ወደ ግሪክ የሚደረገው ጉዞ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ተጨማሪ በረራዎች ለማድረግ መወሰኑን ነው የገለጹት ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ፈጣን እድገት ያለው አየር መንገድ ሲሆን በሰባ አምስት ዓመታት የስራ ጊዜ ውስጥ በውጤታማነት እና በአሰራር ስኬት ተወዳዳሪ የሌለው ከአህጉሪቱ ግንባር ቀደም ተሸላሚዎች አንዱ ሆኗል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአምስት አህጉራት ከሚገኙ ከ130 በላይ አለም አቀፍ የመንገደኞች እና የእቃ ማጓጓዣ መዳረሻዎች በመሆን የፓን አፍሪካ የመንገደኞች እና የካርጎ አውታር የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ሲል ዓለም አቀፍ የንግድ አቪዬሽን፣ አየር መንገድ እና የጉዞ የዜና ምንጭ አስነብቧል፡፡