የኢፌዴሪ አየር ሀይል አብራሪዎችን እያስመረቀ ነው

131

ሰኔ 18 ቀን 2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል “ነብሮች 2014” በሚል መሪ ቃል ያሰለጠናቸውን አብራሪዎች እያስመረቀ ይገኛል።

ተመራቂዎቹ በተለያዩ አውሮፕላን አይነቶች በጀማሪነት እና ተጨማሪ አብራሪነት ስልጠና የወሰዱ ነባር አብራሪዎች ናቸው።

በአየር ኃይል አካዳሚ እስከ 4 ዓመታት ስልጠና የወሰዱ ጀማሪ አውሮፕላን አብራሪዎችን ጨምሮ የተለዬ አብራሪነት ስልጠና የወሰዱም አብራሪዎች ናቸው።

ከተመራቂዎቹ መካከልም በተዋጊ አውሮፕላን ፣ በትራንስፖርት አውሮፕላን፣ በትራንስፖርት ሄሎኮፕተር፣ ቪ አይፒ ሄሎኮፕተር እንዲሁም በመጀመሪያ ደረጃ በረራ ማሰልጠኛ አውሮፕላን አብራሪነት የሰለጠኑ ናቸው።

በቢሸፍቱ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መመሪያ የፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናትና የመከላከያ የጦር ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት ነው ምርቃቱን እያካሄደ ያለው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የመከላከያ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በተገኙበት በመከናወን ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ