የአፍሪካ ልማት ባንክ በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ረገድ ከኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት ይሰራል

278

ሰኔ 17 ቀን 2014(ኢዜአ) የአፍሪካ ልማት ባንክ በክህሎት ልማት፣ በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ ድጋፍና ተደራሽነት እና መሰል የትብብር መስኮች ላይ የኢትዮጵያ ልማት አጋር ሆኖ እንደሚሰራ አረጋገጠ፡፡

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ከአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱል ካማራ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ሚኒስትሯ "በውይይታችን ባንኩ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ጋር በትብብር የሚሰራበት ማዕቀፍን ተመልክተናል" ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል፡፡

ወ/ሮ ሙፈሪያት የአፍሪካ ልማት ባንክ በክህሎት ልማት፣ በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ ድጋፍና ተደራሽነት እና መሰል የትብብር መስኮች ላይ ባንኩ የልማታችን አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል አረጋግጠውልናል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም