ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የአዲስ አመት በዓልን በጋራ እያከበሩ ነው

128
አዲስ አበባ መስከረም 1/2011 ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የ2011ዓ.ም አዲስ አመት በዓልን በጋራ እያከበሩ ነው፡፡ የኢትዮጵያን የ2011ዓ.ም ዘመን መለወጫ በአል ሁለቱ አገራት በዛላንበሳ በጋራ እያከበሩ ይገኛሉ፡፡ በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎች የሁለቱ አገሮች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡ በክብረበዓሉ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ተገኝተዋል፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ እንዲሁም የሁለቱ አገሮች ዘላቂ ሰላም በሁለቱ ህዝቦች ተሳትፎ የሚረጋገጥ መሆኑን ተናግረዋል። ሁለቱ አገሮች በዓሉን በጋራ ያሳፉት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር በማለም እንደሆነ ተገልጿል። ለአመታት ሻክሮ የቆየው የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት በሁለቱ አገሮች መሪዎች ቁርጠኝነት የተነሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠንካራ ሊሆን ችሏል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም