ለመጪው ትውልድ የምናስረክባት ኢትዮጵያ ሁሉም በሰላም የሚኖርባትና ለምለም ምድር ለማድረግ አብረን እንቁም -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

172

ሰኔ 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመጪው ትውልድ የምናስረክባት ኢትዮጵያ ሁሉም በሰላም የሚኖርባትና ለምለም ምድር ለማድረግ አብረን እንቁም ሲሉ ገለፁ፡፡

ይህ የጁምዓ ዕለት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ነፍሱን በይቅር ባይነት አንጽቶ፣ ልብሱንም በመልካም መዓዛዎች አጥርቶ በፈጣሪው ቤት የሚሰባሰብበት የተወደደ ዕለት ነው ብለዋል።

“የተከበራችሁ ሙስሊም ወገኖቼ ይህ ዕለት ለሀገራችን ሰላም የምትጸልዩበት እንዲሁም ለትውልድ የሚተርፍ መልካም አሻራችሁን የምታሳርፉበት እንዲሆን ጥሪ እያቀረብኩ፤ ለመጪው ትውልድ የምናስረክባት ኢትዮጵያ ሁሉም በሰላም የሚኖርባትና ለምለም ምድር ለማድረግ አብረን እንቁም” እላለሁ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።