በአማራ ክልል በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኝ ለተከላ ተዘጋጅቷል

84

ሰኔ 17/2014/ኢዜአ/ በአማራ ክልል በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኝ ተከላ በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል።

በክልሉ የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም በጎንደር ክተማ አዘዞ መድሃኒያለም ቀበሌ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ሃላፊዎች በተገኙበት ተጀምሯል፡፡

በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ፣የቀድሞው የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል የክልል አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተጀምሯል።

በዚህ የክረምት ወቅትም ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዩን በላይ ችግኝ ለተከላ ተዝጋጅቶ በዛሬው እለት በይፍ ተከላ ተጀምሯል።

በክረምት ወቅት ከሚተከሉ ችግኞች መካከልም ከ13 ነጥብ 4 ሚሊዩን የሚልቀው አትክልትና ፍራፍሬ መሆኑ ተመላክቷል።

በክልሉ ባለፈው አመት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን በላይ ችግኝ በመትከልም በህብረተሰቡ በተደረገ እንክብካቤ 84 በመቶ ማጽደቅ እንደተቻለም ተገልፇል።

እንዲሁም በ2012 በተደረገ የ1 ነጥብ 5 ቢሊዩን ችግኝም 76 ነጥብ 4 በመቶ በማጽደቅ የክልሉን የደን ሃብት ሽፋን ማሻሻል እንደተቻለ ተብራርቷል ።

የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙም የደን ሃብት ሽፋኑን ለማሻሻል ከማስቻሉም በላይ ደርቀው የነበሩ ምንጮች መልስው ውሃ እንዲይዙ በማድረግ ለመስኖ ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠርም አስችሏል።

በጎንደር ከተማ የተጀመረው  የችግኝ ተከላ በቀጣይ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም