በሰብዓዊ ልማት ላይ ያተኮሩ የጓሮ ግብርና ሥራዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው

205

ሰኔ 12 ቀን 2014 (ኢዜአ)በሰብዓዊ ልማት ላይ ያተኮሩ የጓሮ ግብርና ሥራዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

''ዛሬ በአዲስ አበባ በመከናወን ላይ የሚገኙና በሰብዓዊ ልማት ላይ ያተኮሩ የጓሮ ግብርና ሥራዎችን እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች ለመመገብ የሚያስችሉ የምገባ ማዕከላትን ጎብኝተናል'' ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

አክለውም እንደዚህ ያሉት ሥራዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው፤በመሆኑም በሁሉም አካባቢዎች በስፋት ሊከናወኑ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም